የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከክፍለ ከተማው የንግድ፣ ህብረት ስራ እንዲሁም ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ጋር የተዘጋጀው የህዝብ የእንጠያየቅ መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ታሪክ የብልጽግና መንግስት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስት በመሆኑ ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ውብ፣ ምቹና ማራኪ የስራ፣ የመኖሪያና የቱሪዝም ማዕከል ማድረግ እንደተቻለ በማብራራት ይህ የልማት ስራ የበለጠ እንዲሰፋ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ስላለባቸውና የህዝብን ጥያቄዎች በየጊዜው በመቀበል ችግሮችን እየለዩ ለመፍታት ያስችል ዘንድ ይህንን አይነት የእንጠያየቅ መድረክ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን በመግለጽ፣ ህዝቡም በግልጽ ጥያቄዎቹን ማቅረብ እንዳለበት ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ በበኩላቸው መድረኩ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ተሳትፎ በማጠናከር ህዝቡ በተለያዩ ጊዜያት ለሚያነሳቸው የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንዲያገኝ እድል የሚሰጥ ከመሆኑ ባሻገር በመንግስትና በህብረተሰቡ መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ለተሻለ አፈጻጸም የጎላ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በመድረኩ የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ከአሥራ አንዱም ወረዳዎች የተውጣጡ የሐይማኖት አባቶች፣ ሙህራን፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የወጣቶች እና ሴቶች አደረጃጀት ተወካዮች፣ የጥቃቅን እና አነስተኛ አንቀሳቃሾች፣ የእድር ምክር ቤት ተወካዮች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ተገንኝተዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.