ከተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ

ስምምነቱን ከ12 የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተከናወነ ሲሆን በአገልግሎት አሰጣጡ መሻሻሎችን ለማስመዝገብ እና በቅንጅት ለመስራት በሚያስችሉ ተግባራት ላይ በእቅድ ለመስራት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር ባደረጉት ንግግር እንደ ሀገር፤ እንደ ከተማ በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ላይ የሚታይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እና የህዝብን እርካታ ለማረጋገጥ እንዲቻል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ 

በቅንጅት ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የአገልግሎትና ቴክኖሎጂ ክላስተር አሰራር እቅድ ያቀረቡት የቢሮው አማካሪ አቶ አቡበከር ሀሺም በበኩላቸው የቅንጅታዊ አሰራሩ የትኩረት መስክ የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታልይዝ በማድረግ የአገልግሎት ቅልጥፍና እና ተደራሽነት በማስፈት የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ 

በቅንጅት ለመስራት የተፈራረሙት የተቋማቱ የስራ ሀላፊዎች እንደገለፁት በቅንጅት ለመስራት ከተያዙት እቅዶች መካከል ቴክኖሎጂ መር አገልግሎት የመስጠት ስራ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን የማሻሻል ተግባር በተቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆኑን አንስተው ቴክኖሎጂዎችን ለማልማት እና ለማስተግበር የተጠናከረ ክትትልና ግምገማ አስፈላጊ ነው ብለዋል። 

በመጨረሻም ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በትኩረት በመወጣት በአገልግሎት አሰጣጡ ተፈላጊውን ለውጥ ለማምጣት መስራት ይገባል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.