የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክረው የህንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል

ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በተለይም በአዲስ አበባ  ፒያሳ የሚገኘውን የጥቁር ህዞቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆነውን የአደዋ ድል መታሰቢያ የጎበኙ ሲሆን  የጣሊያንን ወራሪዎች በቆራጥነት  ድል ለነሱ  ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ክብር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል 

የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በጉብኝታቸው በአድዋ መታሰቢያ ውስጥ የሚገኘውን የአርበኞች መታሰቢያ ሀውልቶችን እና ቅርሶች  የያዘውን ዘመናዊ የአደዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም  መጎብኘታቸው ተጠቅሷል ።

ጉብኝቱ የህንድ እና የኢትዮጵያ የቀደመእና ታሪካዊ ሁለንተናዊ ግንኙነት  ይበልጥ እንደሚያጠነክረው ተዘግቧል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.