“ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ በከተማችን የብክለት መከላከል ንቅናቄ አስጀምረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ተፈጥሮ ለአዲስ አበባ የለገሳትን ውበት ያመናመነውን አሰራር ለመቀየር እና የከተማውን ሰርዓተ ምህዳር ለማሻሻል የሚረዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ርብርብ ፣ በልዩ የአመራር ትኩረት እና በአጠረ ጊዜ ተፈጽመዋል።

ከፍተኛ ለውጥ እያመጡ ካሉት ፕሮጀክቶች መካከል ዋነኞቹ ለሞቱት የከተማዋ ወንዞች ትንሳኤቸውን፤ ለተበከሉት ደግሞ ህክምናን ያበሰረው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት አንዱና መሰረታዊ ሲሆን በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ የነበረውን የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን የታደገውና ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 15 በመቶ ያሳደገው የአርንጓዴ አሻራ ማኖር ኢኒሼቲቫችንም ተጠቃሽ ነው።

የተሰሩት ስራዎች አዲስ አበባን የቱሪስት መዳረሻና ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ያደረጓት ቢሆንም አሁንም ድረስ የድምጽ እና የፍሳሽ ብክለት እና አወጋገድ የከተማችን ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል።

በሕግና በአሰራር ችግሩን ለመፍታት ከምናደርገው ጥረት ባሻገር ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመስራት ለውጥ ለማምጣት ንቅናቄውን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.