ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ የሆነችው አዲስ አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ የሆነችው አዲስ አበባ

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ  እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎች  አማራጭ ባለማግኘታቸው ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪን መንገድ የሚሻሙ ነበሩ።  ዛሬ ይህ  ታሪክ ሆኖ አልፏል ።

ችግሩን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ  ለታዳጊዎች ፣ ለወጣቶች እና ለህፃናት ምቹ ከተማን ለመገንባት በመወሰን የከተማዋ ጎዳናዎች ለሁሉም ተስማሚ እንዲሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን አከናውኗል ።

ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች  ሁሉን በመልኩ አድርገው በእግረኛና በሳይክል መንገድ ተውበው ፣ በአረንጓዴ አበቦች አጊጠው ለእግር ጎዞዎች እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ምቹ ሆነዋል።

አሁን ላይ በአዲስ ጎዳናዎች ሲጓዙ  በተመቻቸላቸው ጎዳናዎች እና ቦታዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ  ወጣቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋውያን እና ጎልማሶችን  መመልከት የተለመደ ባህል ሆኗል ።

ምቹ ንፁህ ጤናማ ለሁሉ ተስማሚ ከተማ አዲስ አበባ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.