"ከተማዋ በአረንጓዴ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ከተማዋ በአረንጓዴ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተማማኝ የሆነ ዕድገት እያሳየች ትገኛለች፡፡ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚኣብሄር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ አመራር;ሰራተኞች፣ መዋቅር እና በጎ ፍቃደኞች የችግኝ መንከባከብ መርሀ ግብር አካሔዱ።

በችግኝ መንከባከብ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚኣብሄር እንደገለፁት ካለብን ሃገራዊ የሙያ ኃላፊነት ባሻገር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን የችግኝ እንክብካቤ አንዱ ነዉ ብለዋል።

በዓለም ደረጃ በትላልቅ መድረኮች ሳይቀር የአረንጓዴ አሻራ የልማት ስራችን እዉቅናን በመጎናፀፍ ለሽልማት መብቃት መቻሉን አስታዉሠዉ ከተማዋ በአረንጓዴ አሻራ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስተማማኝ የሆነ ከፍታ እያሳየች ትገኛለች ሲሉም ገልፀዋል፡፡

አክለዉም ከክብርት ከንቲባችን ጋር በጋራ በመሆን የተከልናቸዉን ችግኞች መትከል ብቻ ሳይሆን መከታተል እና መንከባከብና ከእኛ ምንግዜም የሚጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ ያሉት የቢሮዉ ኃላፊ በየአካባቢያችን የሚገኙ ችግኞችን መንከባከብና መጠበቅ ለነገ ሀገር ተረካቢ ትዉልድ የምናወርሰዉ ሀብት ጭምር ነዉ ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት እና በስሩ ያሉትን የመዋቅር አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም በጎ ፍቃደኞችና ሌሎች አካላትን በማስተባበር ከኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በቅንጅት ላካሔደዉ ስኬታማ የችግኝ መንከባከብ ስራ በቢሮዉ ስም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.