የህብረት ስራ ማህበራት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህብረት ስራ ማህበራት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

የፌደራል ኅብረት ስራ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ኅብረት ስራ ኮሚሽን በጋራ   ዘላቂ የገጠር  ትስስር በመፍጠር  የገጠር ከተማ  ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ  ትስስር እናረጋግጣለን በሚል መርህ የገበያ ትስስር መድረክ አዘጋጅተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ የህብረት ስራ ማህበራት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

መንግስት  ካስቀመጣቸው ግቦች አንዱ የመቀነስ  ግብ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር የኑሮ ውድነትን  ለመቀነስ የመሰረተ ልማት ማቅረብ፣ ማምረት እና መግዛት  ዋና ዋናዎቹ መፍትሄዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ይህን ለማሳካት የመሰረተ ልማት አቅርቦት በማሳደግ፣ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት እንዱሁም የሰንበት ገበያዎችን በማስፋት ለህብረት ስራ ማህበራት ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 

 አቶ ጃንጥራር  አክለውም ማህበራትን   ከክልል  ዩኔኖች ጋር በማስተሳሰር መጠነ ሰፊ ምርቶች ወደ ከተማችን አዲስ አበባ ማስገባት እንደተቻለ  ገልጸው በቀጣይ ወራትም ህብረት ስራ ማህበራት   ምርቶችን በብዛትና በጥራት   ለህብረተሰቡ  አንዲያቀርቡ  አሳስበዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ  በበኩላቸው የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ጋር በመቀናጀት በርካታ ምርቶችኝ ለከተማ አስተዳደሩ እያቀረቡ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር  በመቀናጀት ምርቶችን በስፋት እንደሚያቀርቡ  ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ኅብረት ስራ  ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታየ  መሀመድ በበኩላቸው  በአምራችና  በማህበራት መካከል የገበያ ትስስር በመፍጠር   ምርቶችን በብዛት፣በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ  ማቅረብ እንደተቻለ ገልጸው በቀጣይም በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ምርቶችን በስፋት ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልጸዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.