ሰውን ማዕከል ያደረጉ፣ ለሰው ክብር ቅድሚያ የሚሰጡ፣ ፈርጀ-ብዙ የከተማዋ ፕሮጀክቶች የታለመላቸውን ግብ እያሳኩ ነዉ።
ሴቶችን በኢኮኖሚ ማሳደግ፣ ሁለንታናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ፣ መሆኑን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በችግር ውስጥ ያሉ ሴቶችን በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በማካተት፣ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ አይነተኛ ማሳያው ደግሞ ሰውን ማዕከል ያደረገዉ እና ለሰው ክብር ቅድሚያ የሚሠጠዉ የጉለሌ የተቀናጀ ልማት መንደር አንዱ ነው ፡፡
በዚህ መንደር እራሳቸውን ለአውሬ እና ለተለያዩ አደጋዎች አጋልጠው፣ እንጨት ከጫካ በመልቀም ይተዳደሩ የነበሩ፣ እንዲሁም የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን ይቸገሩ የነበሩ ሴቶችን በማሰባሰብ እና አሰቃቂ ከነበረው የዕለት-ከዕለት ስራቸዉ በማውጣት፣ የራሳቸውን ስራ መስራት እንዲችሉ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
ምንም ገቢ የሌላቸው እና የኑሮ ጫና የበረታባቸው፣ በዚህም ለአስከፊ ህይወት ተጋላጭ የነበሩ እናቶች፣ በእንጀራ ማእከል፣ የወተት ማእከል እና በምገባ ማእከል ስራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ የራሳቸው እና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት መቀየር እንዲችሉ ማድረግም ተችሏል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ የተገነባው ይህ የጉለሌ የተቀናጀ ልማት መንደር፣ የመኖሪያ መንደር፣ የህፃናት ማቆያ የእንስሳት ማርቢያ ፣የከተማ ግብረና ቦታዎች ፣የእህል ማከማቻ፣ ወፍጮ ቤት እና መመገቢያ አዳራሽ እንዲሁም ዘመናዊ የአስፓልት መንገድ ያለው ሲሆን፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የሚተዳደሩበት እና የከማችንን ሴቶች በመታደግ የታለመለትን ዓለማ እያሳካ የሚገኝ ሌለኛዉ ትሩፋት ነዉ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.