የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በዛሬው ዕለት 16 ሞዴል ወረዳ ጽ/ቤቶቹን አገልግሎት አስጀምረ።

ኤጀንሲው በዛሬው ዕለት 16 ሞዴል ወረዳ ጽ/ቤቶቹን አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን የአገልግሎት ቀን መሆኑንም ይፋ አድርጏል 

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በያዘው ተቋማዊ ሪፎርም ፕሮግራሙ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና አገልግሎትን ማዘመን ዋነኛ ግቡ አድርጎ እየሰራ ያለ ሲሆን በዛሬው ዕለት በሶስተኛ ዙር በጉለሌ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በቂርቆስ፣ በአዲስ ከተማ፣ በለሚ ኩራ እና በልደታ ክ/ከተሞች 16 ሞዴል ወረዳዎችን ስራ አስጀምሯል። 

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ ስምንት ተገኝተው ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አዲስ አበባ ዋና ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን ሲሆኑ ኤጀንሲው በተቋም ግንባታ የስራ አካባቢን ምቹ በማድረግ የህዝብ እርካታ እስኪረጋገጥ አገልግሎትን ማቀላጠፍ ላይ ትኩረት አድርጓ መስራት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ መልዕክት አሰተላልፈዋል።  

በዚሁ ዕለትም ተቋሙ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን የስራ ሰዓት መሆኑን ይፋ ያደረጉ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ አማራጮቹም ሙሉ ለሙሉ ወደ ቴሌ ብር የዲጂታል ስርዓት መሸጋገሩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ገልፀዋል። 

በተለያዩ ክ/ከተሞች የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ጽ/ቤቶቹን አገልግሎት ያስጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ወራት ማጠቃለያ በሃገራችን የመጀመርያ የሆኑና በርካታ ቴክኖሎጂዎችን ያካተተው የኤጀንሲው ዘመናዊ መሰረተ ልማት እንዲሁም በሁሉም ወረዳ ጽ/ቤቶች የሚገጠመው የካሜራ ቁጥጥር ስርዓት ከከተማው ITDB ቢሮ ጋር በመሆን ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባና የ40 ወረዳዎች የነዋሪ መረጃም ዲጂታላይዝ ሆኖ እንደሚገባደደ ተነግሯል።  

ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር 70 ወረዳዎች ማዘመኑ ይታወሳል።

ለተሻለ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት እንተጋለን!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.