በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ የመሪ ሎቄ አካባቢ ለህዝብ ሁለገብ አገልግሎት የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ይህ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳይ ሲሆን፤ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ፣ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣ ለውድድር፣ ለዕረፍትና ለህጻናት መጫወቻነት ምቹ ሆነው የተገነቡ ናቸው። ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ በ10.5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ለከተማችን ጽዳትና ውበት ተጨማሪ አቅም የፈጠረ ድንቅ ስራ ነው።
በውስጡ ያካተታቸው፦
• ሁለት ዘመናዊ የአዋቂዎችና የህፃናት እግር ኳስ ሜዳዎች።
• የቅርጫት ኳስ፣ የቴኒስና የመረብ ኳስን አጣምሮ የያዙ ሁለገብ ሜዳዎች።
ለተፈጥሮ አድናቂዎች፦
• በተፈጥሮ ድንጋይ ያጌጠ አስደናቂ ፋውንቴንና ፕላዛ፣
• በማራኪ አበባዎች ያማረ አረንጓዴ ስፍራ፣
• ጸጥ ያሉ የማንበቢያ ቦታዎች እና ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች።
• ሙሉ የመጫወቻ ቁሳቁስ የተገጠመለት የህጻናት ማልሚያ (ECD)።
• ዘመናዊ ካፌቴሪዎች።
• ከ400 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ።
• ለኤሌክትሪክ መኪኖች የኃይል መሙያ (EV Charger)።
• የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች
• አካባቢውን በስዕልና በቀለም ያስጌጡ የጥበብ ስራዎች ወዘተ ተካትተዉበታል ።
ይህ ፕሮጀክት ያረፈበት መሬት፣ በደላሎች እጅ የነበሩ 23 ህገ-ወጥ ካርታዎችን በማምከን መሬቱ መልሶ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል የተደረገበት ነው። በተጨማሪም የአካባቢው ነዋሪዎችና ወጣቶች በስራ ዕድል ተደራጅተው የፕሮጀክቱ ዋነኛ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።
መዲናችንን በየዕለቱ እየለወጥን፣ ቃላችንን በተግባር እያረጋገጥን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.