አዲስ አበባን ስሉጥ ከተማ (Smart City)...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባን ስሉጥ ከተማ (Smart City) የማድረግ ውጤታማ ጉዞ!

የስሉጥ ከተማ መገለጫ የሆኑትን ዘመናዊ ተቋማት የመገንባት ህልም እውን ለማድረግ እንዲያስችል፣ ተቋማት አገልግሎታቸውን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ ይኸውም፣ በህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘንድ ይስተዋል የነበረውን እንግልት ለማስቀረት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ 
 
በተለይም ተቋማት አገልግሎታቸውን ከሰው ንክኪ  የራቁ  እና  ለህዝብ ፍትሃዊ  አገልግሎት ማቅረብ  እንዲችሉ በቴክኖሎጂና  በመሰረተ ልማት የታገዙ፣ እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት  እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ሲሆን፣ በዚህም  ለሁሉም ምቹ የሆነች ስማርት ከተማን መፍጠር ተችሏል፡፡

ለአብነትም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልሎት፣ በወሳኝ ኩነት ፣  በሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ፣ በፍቃድ አስጣጥና እድሳት፣ የገቢ አሰባሰብን  እና በትላንትናው ዕለት የተመረቁት ዘመናዊ የፓሊስ ማዕከላትን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤  አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ በማሳደግ  ከዚህ ቀደም የሚስተዋለውን እንግልትን በማስቀረት የህዝብ ሀብት እንዳይባክን አድርጓል፡፡ 

አዲስ አበባን ስሉጥ  ከተማ (Smart City) ለማድረግ የተጀመረው ርዕይ፣  አሁን ላይ በርካታ የህዝብ አገልግሎቶች  በቴክኖሎጂ የታገዙና የተደራጁ እንዲሆኑ በማድረግ ከተማዋን ዘመናዊ ምቹ እና ለሁሉም ተስማሚ እንድትሆን አስችሏል፡፡ 

አዲስ አበባን ለማልማት፣ ሁሉንም የልማት አማራጮች በመዘርጋት ነዋሪዎቿ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል የምንግዜም ተቀዳሚ ተግባር ሆኖ ይቀጥላል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.