"የተሟላ የተቋም ግንባታ መፍጠር በሃገራችን የሚ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የተሟላ የተቋም ግንባታ መፍጠር በሃገራችን የሚታየዉን የፖለቲካ ስብራትን ለመጠገንና ትዉልድን በተሻለ ገንብቶ ለማሻገር የሚያስችል ቁልፍ ጉዳይ ነዉ" አቶ ሞገስ ባልቻ

"ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ" በሚል መሪ ቃል ከከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በዛሬዉ እለት ስልጠና ተሰጥቷል

የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በስልጠናው ላይ እንደተናገሩት ፦መንግስት ለጀመርነዉ ጠንካራ ፓርቲ፤ጠንካራ መንግስትና ሀገረ-መንግስት ግንባታ ስልጠናዉ ጉልህ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡

ኃላፊዉ አክለዉም ለተሟላ ተቋም ግንባታ ወሳኝ ከሆኑት ዉስጥ ዋነኞቹ ጠንካራ አደረጃጀትና የስራ ስምሪት፤የተሻለ የአሰራር ስርዓት እና በቂ የሰዉ ሃይል መኖር መሆኑን ገልፀዉ በእነዚህ ላይ በሙሉ አቅምና እዉቀት ተግተን በጋራ ከሰራንና ሃላፊነታችንን ከወዲሁ ከተወጣን የሀገራችንን ብልጽግና እናረጋግጣለንሲሉ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ስነ-ምግባር ኮሚሽን ሃላፊ ወ/ሮ መሬማ ደሊል በበኩላቸዉ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በየጊዜዉ አደረጃጀቱንና አሰራሩን እየፈተሸና ክፍተቶቹን እየሞላ በመምጣቱ ከችግሩ ተላቅቆ እስከ ወረዳ ድረስ በመዉረድ ተግባርና ሃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ገልፀዉ እንደሃገር አቀፍም ተሞክሮ ሊወሰድበት የቻለ ተቋም በመሆኑ አመራሩ በዚህ ስልጠና በቂ ግንዛቤና እዉቀት የሚያገኝበትና ሃላፊነቱን የሚወጣበት ነዉ ብለዋል፡፡

የስልጠናዉ ተሳታፊ አመራሮችም ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር እና የፓርቲያችንን ተልእኮ በተገቢዉ ለመወጣት ከአመራር እስከ አባላትና ደጋፊዎች ጭምር ሃላፊነትና ግዴታን ያስጨበጠ ስልጠና በመሆኑ በቀጣይ ይህን ወደ መሬት በማዉረድ ፓርቲያችንን እና ህዝባችንን ለማገልገል ተግተን በጋራ እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.