በኮልፌ ክፍለ ከተማው አስተዳደር የ2018 የገና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በኮልፌ ክፍለ ከተማው አስተዳደር የ2018 የገና በዓል አስመልክቶ ኢግዚብሽንና ባዛር በይፋ ተከፈተ፡፡

" እምርታ ለዘላቂ ከፍታ " 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ባደረጉት ንግግር አስተዳደሩ የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትና ምርትና ምርታማነትን በማሻሻል ረገድ ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑን የገለፁ ሲሆን የገና በዓሉን ምክንያት በማድረግ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅኦ መቅረቡን በስፍት መቅረቡን ተናግረዋል::

የብልፅግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሚ ሙሄ አሊ እንደተናገሩት የተከፈተውን ባዛርና ኤግዚቢሽን በአይነትም በይዘትም የተሻለና ለሸማቹ ማህበረሰብ የተለያዪ የምርት አይነቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በአሉን በተረጋጋ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገና በአል ምክንያት በማድረግ በጦር ሀይሎች አደባባይ  ኤግዚብሽንና ባዛር የተከፈተ ሲሆን በኤግዚብሽኑ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ከ70 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች፣ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የሚሰሩ ነጋዴዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በኤግዝብሽኑ በርካታ የባህል አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ማርና የማር ውጤቶች፣ እንጨትና ብረታብረት  ውጤቶች፣ የኢንደስትሪ ምርቶች ፣ የግብርና ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሌሎች ለበአል የሚውሉ የተለያዩ  ምርቶች ቀርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.