የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገና በዓልን አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገና በዓልን አስመልክቶ ባዛርና ኤግዚቢሽን ላይ በቂ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው በባዛር መክፈቻው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ለበዓል ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት ለማህበረሰብ በማቅረብ የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ ያለው ሚና ጉልህ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው  ለበዓል የሚሆኑ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርት በስፋት በማቅረም አምራችና ሸማች ላይ ያለው ሰንሰለት በማሳጠር ውጤታማ ስራ መሰራት መቻሉን ገልፀዋል።

የገና በዓል በማስመልከት የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጠነ ዋጋ ማቅረብ  መቻሉን የገለፁት ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳውአያይዘው ለአምራቾችም ምርታቸውን ለመሸጥ እድል የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንዳሉት ለመጪው የገና በዓል የምርት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማህበረሰብ በስፋት ማቅረብ መቻሉን ገልፀዋል።

ባዛርና ኤግዚቢሽን የተለያዩ ምርቶች በስፋትና በጥራት እየቀረቡ በመሆኑ የገለፁት ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ባዛሩ ለሸማቹ ማህበረሰብ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት የላቀ አስተዋፆ እንዳለው አንስተዋል።

ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ አክለው የቅዳሜና እሁድ ተሳትፎን በብዙ አልቃችሁ ለነዋሪዎቻችን ምርቶችን ተደራሽ ለማድረግ የላቀ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።

በባዛሩና በኤግዚብሽኑ ከቀረቡ ምርቶች መካከል የግብርና የኢንዱስትሪ ምርቶች፣አልባሳት፣ የባልትና ውጤቶች እንዲሁም ለበዓል ፍጆታ የሚሆኑ ግብዓቶች በስፋት ቀርቦዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.