የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በመዲናችን የንባብና የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በመዲናችን የንባብና የምርምር ባህል ማዕከል ሆኖ ስራ ከጀመረ እነሆ አራተኛ ዓመቱን ይዟል።

ዛሬ ማለዳ በቤተ-መጻሕፍቱ በመገኘት፣ ተቋሙን ወደ ላቀ የዲጂታል ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ሦስት ታላላቅ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን በይፋ አስጀምረናል።

በዓመት በአማካይ ለ1.8 ሚሊዮን አንባቢዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ይህንን ተቋም ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችሉ፦ የተቀናጀ የቤተ-መጻሕፍት አስተዳደር ሥርዓት፣ ዘመናዊ የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና ዓለም አቀፍ የምርምር መድረክ (Research Portal) በይፋ ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል።

እነዚህ አገልግሎቶች አብርሆት በአዲስ አበባ ብቻ የተገደበ እንዳይሆን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ሲሆን፤ ማንኛውም ተማሪም ሆነ ተመራማሪ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ  ሆኖ የአብርሆትን የዕውቀት ማዕድ መቋደስ እንዲችል ያደርጋሉ።
በተጨማሪም የታሪክ ሰነዶቻችን በዲጂታል መንገድ ተጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፉ ትልቅ እገዛ ይኖራቸዋል።
እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በማልማት አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ባለድርሻ አካላትን በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.