በመዲናዋ በሁሉም የገበያ ማዕከላት እና የሰንበት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ በሁሉም የገበያ ማዕከላት እና የሰንበት ገበያዎች እና በባዛሮች በተሠራዉ የቅድመ ዝግጅት ስራ በቂ የምርት አቅርቦት እና ፍትሀዊ የግብይት ስርዓት መኖሩ ተገለፀ

በመዲናችን የገናን በአል ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ በሁሉም የገበያ ማዕከላት እና የሰንበት ገበያዎች በተሠራዉ የቅድመ ዝግጅት ስራ በቂ የምርት አቅርቦት  እና ፍትሀዊ የግብይት ስርዓት መኖሩ ተገለጿል።

 መጭውን  የገና በዓል በማስመልከት  የህብረተሰቡን የፍጆታ ፍላጎት ለማሟላት እና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ  የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት ዉጤቶች በመዲናዋ በ 5ቱ  የገበያ ማዕከላት እና ከ220 በላይ ሰንበት ገበያዎች ላይ  በስፋትና በጥራት የቀረቡበትና  ሸማቹም በተመጣጣኝ ዋጋ   የሚገበይበት  ፍትሀዊ የግብይት ስርዓት  መፈጠሩ  በየደረጃዉ ያለዉ የመንግስት አካላት ከአምራቹና ከነጋዴዉ ጋር  ተቀናጅቶ በመስራቱ ነዉ ተብሏል።

ይህን ጤናማ የግብይት ስርዓት የበለጠ ለማስቀጠል የህገወጥ ነጋዴዎችንና ደላሎችን አሻጥር እና ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል ከገቢያ ማረጋጋት ግብረ ሃይል እና ከፀጥታ አካሉ ጋር ሁሉም የከተማዋ ማህበረሰብ በኃላፊነት ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን  ከተማ አስተዳደሩ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ  ከተለያዩ መዋቅሮች ጋር  በጋራ እየሠራ ያለዉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ከሰንበት ገቢያዎች በተጨማሪ በስፋት ዘይት፣የስንዴ ዱቄት፣ እንቁላል እንዲሁም ስኳር  በከተማዋ በሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት በኩል የቀረቡ በመሆኑ ሸማቹ ማህበረሰብ በአቅራቢያው በሚገኙ የገበያ ማዕከላት፣  የሰንበት ገበያዎች እና ኤግዚቪሽንና  ባዛር   በመሄድ የሚፈልጉትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ ጥረ ቀርቧል።

በዓሉን አስመልክቶ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም እየተሰራ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባር በማድነቅ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በግብይት ወቅት ሲሸምቱ የነበሩ  የከተማዋ  ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.