የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ዛሬ በዋዜማው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ዛሬ በዋዜማው 381 ቤቶችን ከሙሉ የቤት ዕቃና ከበዓል ማሳለፊያ ጋር በስጦታ አስረክበናል።

ከእነዚህ ቤቶች መካከል፦ 273ቱ ቀደም ሲል የወዳደቁ የቀበሌ ቤቶች የነበሩ ሲሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው እንደገና በመገንባት  ለቀድሞ ለነዋሪዎች የተላለፉ ናቸው።
108ቱን ደግሞ ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች፤ ለሀገር የአካል ዋጋ ለከፈሉ የጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት፤ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ለሀገር ባለውለታዎች አስተላልፈናል።
ቤቶቹ የሕፃናት መጫወቻን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው፣ አዲስ የተገነቡ ዘመናዊ መንደሮች ናቸው።

ከተማችንን ውብ አበባ ስናደርግ፣ የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ዘይቤ በማዘመን እና የኑሮ ጫናዎችን እያቃለልን ጭምር  ነው ። 

በከተማችን ከለውጡ  ወዲህ በሰው ተኮር እሳቤ እየተመራን የበጎ ፍቃድ ተሳትፎ ባህል እየሆነ  በመምጣቱ  45 ሺህ ቤቶችን በበጎ ፍቃድ ተሳትፎ በመገንባት ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ ወገኖችና ለሀገር ባለውለታዎች በማድረስ እምባቸውን ማበስ ተችሏል።

“ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው” እንደሚባለው፤ ሁላችንም እየተባበርን  ጊዜያዊ ችግሮችን በጋራ በመሻገር  ለዘላቂ ልማት እንተጋለን። 

ለበጎ ፍቃደኞችና ለአስተባባሪዎች በሙሉ  በተለይም የኤን .ኤ ቢዝነስ ቬንቸርስ እና ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያንን  በተጠቃሚዎቹ፣ በከተማው አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ከልብ አመሰግለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይበርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.