የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች ተኪና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን እንዲያመርቱ ጉልህ ሚና አለው፡፡ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ

አውደ ርዕዩን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣የኢፌደሪ ንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት በሚል መሪ ቃል በጊዮን ሆቴል በዛሬው እለት ተከፍቷል፡፡ 

በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት ኢንዱስትሪዎች ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን ጠቁመው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ የአምራች እንዱስትሪዎችን አቅም በማሳደግ፣ ተኪ ምርት በማምረት፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘትና ዘላቂ የሆነ የስራ እድል በመፍጠር አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡ 

በከተማ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በጥራትና በቁጥር ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ ምክትል ከንቲባ ገልጸው፤ አምራች ኢንዱስትሪዎችም ሁሉንም ድጋፍ ከመንግስት ባለመጠበቅ ፈጠራን በማሻሻል የራሳቸውን ጥረት ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ከ200 በላይ አምራች ኢዱስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.