ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን የሚለው ራዕይ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ስለመሆኑ ውጤቶቻችን ማሳያ ናቸው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ

እንደ ሀገር ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስራዎችን እንዲሁም አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያረጋግጥ የብዝሃ ዘርፍ የልማት ስትራቴጂ በመከተል እየሰራናቸው ያሉ ስራዎች በሁሉም መስኮች ፍሬ እያፈሩና የኢትዮጵያን በ2023 አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን በሚል የተነሳንለትን አላማ በሚያሳካ ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆናችንን ያረጋገጠ ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ አስታወቁ፡፡

የኢፌድሪ መንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናት አለም መለሰ ለተለያዩ የሚድያ አካላት የተከናወኑ  ዋና ዋና መንግሥታዊ ሥራዎችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በቢሾፍቱ አቡሴራ የግንባታ ሥራው የጀመረው  የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ እና ሌሎች ሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት ዘመን ማሳያዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን ለመገንባት ኢትዮጵያ በጀመረችው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት በአህጉራችን ከቀዳሚዎቹ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሃገራት ተርታ መሰለፉን አንስተዋል፡፡

መንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ተግባራዊ ካደረገባቸው ጊዜያት አንስቶ የኢኮኖሚ ማነቆዎችን በየጊዜው እየፈታ እንደሚገኝ እና ፡ይህም የምርት አቅርቦትን፣ የመንግሥት ገቢን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን እና የወጪ ንግድን ማሳደግ መቻሉን ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ፣ግብርናን ማዘመንና በማሻሻል፣ የአምራች ኢንዱስትሪውን ለፈጠራና ለፍጥነት ዕድገት ምቹ የሆነ ማዕቀፍ መፍጠር ፣በማዕድን ዘርፍ ሀብቶቻችንን ማወቅ፣ መግለጥና ለኢትየጵያ ብልፅግና ማዋል እንዲሁም በቱሪዝም   ነባር ሀብቶቻችንን "ማስተካከል፣ ማስፋትና ማበርከት" በሚለው መርህ በመመራት የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን የትውልድ ቀጣይነት  እየተገነባባቸው መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

በዲጂታል ኢኮኖሚና የከተማ ልማት ሥራዎችም አስደናቂ ውጤት  የተመዘገበባቸው የኢትዮጵያን ተስፋ እና አቅም ያሳዩ መሆኑን ሚኒስትሯ  በመግለጫቸው አንስተዋል፡:

የያዝነው ዓመት ኢትዮጵያ ሁለት ታላላቅ ሁነቶች፡ ጠንካራ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚረዳ ሀገራዊ ምክክር እና የ7ኛውን ዙር ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂድበት መሆኑም በመግለጫው ተካቷል፡፡ 
የመደመር መንግሥት ሀገራዊ ምክክሩ አካታች እና ውጤታማ ምርጫውም ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ገለልተኛ እና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መግለጫው በአጽንኦት  ገልጾአል፡፡

በመጨረሻም፣ የተመዘገቡት ውጤቶች የመደመር መንግሥት ሕዝብ የተሳተፉበት አካታች የልማት እሳቤን በመከተል ፈጣን ሀገራዊ እድገትን ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ልዕልናን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ በሁሉም ዘርፎች እየሰጠ የመጣው ወሳኝ አመራር ውጤት መሆኑንም መግለጫው አመላክቷል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.