የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የከተማን ግብርናን በማሳደግ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል።
በየካ ክፍለከተማ ከ200 በላይ የሚሆኑ በቤተሰብ ለተደራጁ ኢንተር ፕራይዞች የእንቁላል ዶሮዎች ርክክብ ተደርጓል።
በርክክብ ስነስርአቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ምገስ ባልቻ እንደተናገሩት ይህ መርሃግብር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፈጠሩም ባሻገር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶችና ወጣቶች የተረከቡትን ስራ ተግባር ላይ በማዋል እራሳቸዉን ለዉጠዉ ለሌሎች አርአያ ልሆኑ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
የመርሃግብሩ ተጠቃሚዎችም በበኩላቸዉ የተረከብነዉን የእቁላል ዶሮ ኬጂና መኖ በአግባቡ በመጠቀም ወጤታ ማስራዎችን በመስራት ምርቶቹን ለህረተሰቡ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸዉን ገልጸዋል።
AMN
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.