የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በዛሬው ዕለትም ከሸገር ከተማ ጋር በ6 ወራት በቅንጅት በተሰሩ የፀጥታና የህግ የበላይነት በማስከበር ሂደት የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የጥምቀት በዓል እቅድ ውይይት ላይ የጋራ የምክክር መድረክ ተደረገ።
ከሸገር ከተማ ፀጥታና አስተዳደር ጋር በቅንጅት በመሰራቱ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና በህግና በስርአት የሚመሩ ከተሞችን መፍጠር መቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላም ና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ::
በመድረኩ ላይ በመገኝት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የሁለቱንም ከተሞች አሰራር በማጠናከር በከተማው ላይ እንደ ሀገር የተከናወኑ አለማቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባኤዎች ሁነቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፉ ከማድረጉ ጎን ለጎን ህብረተሰቡን በዋነኝነት የሰላም ባለቤት በማድረግ ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር በጋራ በመሰራቱ ወንጀሎችንና የጸረ ሰላም ሽብር ሀይሎችን ሴራ ማክሸፍ መቻሉን ኃላፊዋ ጠቅሰው
የጸጥታው ስራ ወጥነት ባለው መልኩ እንዲሰራና ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ስምሪት በመስጠት እንደ ቢሮም ደግሞ የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀት በጋራ በማጠናከር ወንጀሎችን ቀድሞ በመከላከል አካባቢን በመጠበቅ ባለፉት ወራት ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለአለም ህዝብ ያሳየንበት ነበርም ሲሉ የተደመጡ ሲሆን የንግድ ስራው ቁጥጥሩን በማጠናከር ህገ ወጥ የንግድ ግብይት እንዳይፈጠር የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ለማድረግ አምራቹና ሸማቹ ማህበረሰብ በቀጥታ እንዲገናኙ የማድረግና የግብይት ስርዓቱ በተቀላጠፈ መልኩ እንዲከናወን በተገቢው መንገድ ከሸገር አስተዳደር ጋር መሰራቱን አንስተዋል
ኃላፊዋ አያይዘውም የህግ የበላይነትን በሁለቱም ከተሞችና ተቋማት ላይ በማስፈንና በርብርብ በመሰራታቸው በህግ የሚመራ ህብረተሰቡ ማፍራት እንደተቻለ ሁሉ የጸጥታው ስራ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎች ቀድሞ በመለየት ከፊታችን የሚከበሩና በከተማና በሀገር ደረጃ የሚሰሩና የሚከናወኑ በዓላት እንዲሁም 7ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲከናወኑ ቀደም ተብሎ ከተሰራው ስራ በበለጠ መልኩ እንድነትንና ቁርጠንነትን በሚያጎለብት መልኩ ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ እንደ መሆኑ መጠን በቀጣይም ቅንጅታዊ ስራዎቻችንን በማጠናከር ለሀገር ሰላም በትብብር በመሆን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል ።
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ዶክተር ተሾመ አዱኛ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው ሸገር ከተማ ከተቋቋመ ጀምሮ እንደ ሀገር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በማስታወስ የሁሉም መነሻና የጥንካሬ መሰረት ከተማ እንደ መሆኑ በዕውቀትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ከተሞች ከተማ እንዲሆኑ በጸጥታው ስራ ላይ ተጠናክሮ በመስራት ዘላቂነትን በማጠናከር የመጣውን ለውጥ አጠናክሮ በማስቀጠል አብሮነታችን ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ የተጀመረውን የትምህርት፣የልማት የሀብት አጠቃቀሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሰላምን በጋራ ጠብቅ ማስኬድ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
በመጨረሻም ሁለቱም ኃላፊዎች መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የተቋማቱን ተግባሮች በማስተዋወቅና በጋራ በመሰራቱ እየታየ ያለውን የጸጥታ አጠባበቅ ስራ የተሻለ ውጤት ያመጣ ስራ በመኖሩ ከጸጥታው ጎን ለጎንም በመልካም አስተዳደር የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት ለሀገር ገጽታ በመገንባት የዜጎችን ሰላም ማረጋገጥ ይገባል በማለት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.