ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ-ጥር ከሆነው ኬርፎር (Carrefour) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓትሪክ ላስፋርገስ እና የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ጋር በከተማችን ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
በውይይታችን ኬርፎር ከሜድሮክ ኢቨስመት ግሩፕ ጋር በፈረመዉ ስምምነት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚገባበትን ምቹ ሁኔታን በመጠቀም፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የንግድ ትስስሮችን ለማጠናከርና ሌሎችም ታዋቂ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ወደ ከተማችን ለማምጣት በጋራ ለመሥራት ተግባብተናል።
አዲስ አበባን የኢንቨስትመንትና የንግድ ማዕከል በማድረግ ተወዳዳሪ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.