የዓለም አቀፉ ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዓለም አቀፉ ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ IShowSpeed የኢትዮጵያ ቆይታ፤ በመላው ዓለም የሚሊዮኖች ዓይኖች ወደ አዲስ አበባ እንዲሳቡ ያደረገ ስኬታማ መርሃ-ግብር ነበር።

ይህ ጉብኝት ከተማችን ያላትን የቆየና የከበረ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣ የከተማችንን ፅዳትና ውበት፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ኩነቱ እስካሁንም መነጋገሪያነቱ የቀጠለ ሲሆን፣ ወደፊትም ብዙዎችን ወደ ሀገራችን ይስባል ብለን እናምናለን።

ይህንን ኩነት በብቃት ላከናወናችሁ ሀገር ወዳድ፣ ጎበዝ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች፣ የግል  እንዲሁም የፌደራልና የአዲስ አበባ መንግስታዊ ተቋማት ልባዊ ምስጋና ይገባችኋል። በተለይም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ ይሳቃል ኢንተርቴይመንት እና ሌሎችም በቅንጅት የሠራችሁ አካላት በሙሉ፤ ያሳያችሁት የላቀ የቅንጅት አቅም እና የሀገር ፍቅር ስሜት 'ይበል' ያሰኛል።
ገና ነው፣ በርቱ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.