የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የኮሪደር ልማት ስራዎችን እና በልማቱ የተነሱ ነዋሪዎችን ጎበኙ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በከተማዋ እየተሰራ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን እና በልማቱ የተነሱ ነዋሪዎችን ተዘዋውሮ ጎበኙ፡፡
በጉብኝት መርኃ ግብሩ ላይ የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በጉብኝታቸው በግንባታ ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፤ በኮሪደር ልማቱ ተነስተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ በሃና ፉሪ እንዲሁም በጉራራ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎችን ጭምር ተዘዋዉረው ተመልክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሪት ፋይዛ መሃመድ ለምክር ቤቱ አባላት እና ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ለማዘመን የመንገድ፣ የመብራት፣ የአረንጓዴ ልማት እና ምቹ የእግረኛ መንገድ እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማት ስራዎችን እተሰሩ ነው ብለዋል።
የተጀመረው የልማት ስራ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲለማ ለማድረግ ምክር ቤታቸው የጀመረውን የክትትልና ድጋፍ ስራም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሪት ፋይዛ መሃመድ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በኮሪደር ልማቱ ተነስተው ምትክ መኖሪያ ቤት በተሰጣቸውን አካባቢዎች ውሃ፣ መብራትና የመንገድ መሰረተ ልማት ከማሟላት ባሻገር የትምህርት እና የጤና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.