ማንኛውንም ዓይነት ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ማንኛውንም ዓይነት ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን በመከላከልና የመቋቋም አቅማችንን በማሳደግ፣ በራሳችን ጥረትና ድካም እየተረዳዳን ለዘላቂ ልማት እንተጋለን።

ልመናና ተረጂነት ስንፍናን የሚያስፋፉ፣ ሰብአዊ ክብርን የሚነኩና ዘላቂ ልማትን የማያረጋግጡ ተግባራት ናቸው።

በመሆኑም የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የግድ ይላል። በተለይም የትምህርትና የሃይማኖት ተቋማት ይህንን የተረጂነትና የልመና አስተሳሰብ በመለወጥ ረገድ ዋነኛ ተዋናይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ይህንን ተግባር ለማሳለጥ የአዲስ አበባ የአደጋ ስጋት ምክር ቤት የአደጋ ተጋላጭነትን በማስቀረት፣ የአደጋ ዝግጁነትን በማጠናከርና ምላሽ ሰጪነትን በማሳደግ በኩል እንደ ሀገር የተጀመረውን የአሰራር ለውጥ ለማስቀጠል ዛሬ ስራውን በይፋ ጀምሯል ። ምክር ቤቱ የተረጂነትን አሉታዊ አስተሳሰብ ለመለወጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥም ግንባር ቀደም ሚናውን ለመወጣት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.