የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበትና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው።

የጥምቀት በዓል  ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀና ፍፁም ባማረ መልኩ በሁሉም ስፍራዎች እንዲከበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር  በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተናል። በውይይታችንም አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ተመልክተናል።

አስተዳደራችን፣ እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ የጥምቀት በዓልም በታላቅ ድምቀትና በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.