የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የመደመር ሀሳብ መንግሥትን፣ የግል ዘርፉን፣ ተፈጥሮን እና የትናንትን ወረት ለነጋችን ብሩኅነት በአንድ ያሰባስባል።

ዛሬ ጠዋት በመረቅነው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ይኽን በግልጽ ተመልክተናል። ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በባሕል፣ በተፈጥሮ እና ታሪካዊ ጥሪቶች የታደለች በመሆኗ ዛሬ ያለንን ጉልበት እና ጥንካሬ ለመጪዎቹ ተከታታይ ትውልዶች በሚተርፍ መንገድ ሀብቶቿን መግለጥ መቀጠል ይኖርብናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.