እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት የመገለጥና  የእርቅና ዳግም የመወለድ ምልክት ነው፡፡በሀገራችን ደማቅ የአደባባይ በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል ድንቅ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች ጐልተዉ የሚታዪበት  ከመሆኑ ባሻገር፤ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ በርካታ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት የሃገራችንን  መልካም ገጽታ ለዓለም የሚያስተዋዉቅ  ደማቅ በዓል ነው።
ይህንን ዉብና ደማቅ በዓል ከሀይማኖታዊ ልዩ ሥርዓታቱ በተጨማሪ ባህላችንን፣ቋንቋችንን ዜማችንን፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በዐደባባይ የምናሳይበት በመሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት ባህል  ሃይማኖታዊ ስረአቱንና እሴቶቹን ጠብቆ በማክበር የበለጠ ሀገራችንን ለአለምእናስተዋቅበታለን።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆን እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.