ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ የጥምቀትን በዓል በሥራ እያሳለፉ ከሚገኙ ጀግና ሠራተኞች ጋር አብረን ምሳ ተመግበናል።
ከአትላስ - ብራስ፣ ከእንግሊዝ ኤምባሲ - ጎላጎል - ኤድናሞል - ፍሬንድሺፕ፣ ከውኃ ልማት - ሩዋንዳ ድልድይ፣ ከቦሌ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት - አያት ሆስፒታል፣ከአደይ አበባ ስቴድየም - ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ እንዲሁም ከኡራኤል -አትላስ መስመሮች እና በካዛንቺስ የሕፃናት ፓርክ (Children’s Park) በዓሉን በሥራ እያሳለፉ ያሉ፣ በተለያዩ ሳይቶች ላይ ሌት ተቀን በመሥራት ለሀገራችን አዲስ የሥራ ባሕል ያስተዋወቁ ጀግኖችን "እንኳን አደረሳችሁ" ብለን አብረን ምሳ ተመግበናል።
እናንተ ጀግና ወጣቶች፤ የሀገር ፍቅራችሁን በጠንካራ የሥራ ባሕል የገለጻችሁ፣ እጅግ ውብና ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት የሚኖርባትን ከተማ እየገነባችሁ ያላችሁ የሀገራችን ተስፋዎች ናችሁ። ከእናንተ ጋር የጥምቀትን በዓል ማዕድ በመጋራታችን እጅግ ደስተኞች ነን።
እንኳን አደረሳችሁ! መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.