የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ በአዲስ አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ በአዲስ አበባ ዘመናዊ የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ከሰንሻይን ፊላንትሮፒ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለአረጋውያን እናትና አባቶቻችን ጋቢ የማልበስና ማዕድ ማጋራት አከናውነናል ።

ከሰንሻይን ፊላንትሮፒ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባስገነባነው  ዘመናዊ የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ማእከል፣ የአገር ባለውለታ የሆኑና ድጋፍ የሚሹ አረጋውያን ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ከተማችን በልማት ሥራዎቿ ሁሉ ታሳቢ አድርጋቸው  በቀሪ ዘመናቸው ለትውልዱና ለሀገራቸው እየጸለዩ እና እየባረኩ በክብር እንዲኖሩ በስፋት እየሰራች ነው። 

ለዚህም  ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለተወጣው ሰንሻይን ፊላንትሮፒ ፋውንዴሽንን እያመሰገንኩ፣ አስተዳደራችን ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ከሚወጡ  ባለሀብቶች ጋር በትብብር ለመሥራት ሁልጊዜም በሩ ክፍት ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.