የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሾን ቢሮ ከኢትዮጽያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሾን ቢሮ ከኢትዮጽያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለዉን የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ::

በዛሬዉ ዕለት የሁለቱ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት  በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የስምምነት ፊርማ አከናዉነዋል።

በስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚዓብሔር እንደተናገሩት ሁለቱ ተቋማት አብረዉ በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ ተገናኝተዉ  መወያየታቸዉን እና የዛሬዉ የስምምነት ፊርማም ይህንኑ መሠረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዉ በከተማዋ ዘርፈ ብዙ የልማት ሰራዎች  እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ነዉ ብለዋል ።

ሃላፊው አክለዉም ስራዎቻችን በብዝሀ ቋንቋን ማዕከል በማድረግ ፤ የከተማችንን ገፅታ  በመገንባት በመንግስት እና በህዝብ መካከል እያደገ የመጣዉን ጠንካራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር  ያለመ ነዉ በማለት አብሮ ለመስራት የተፈጠረዉን እድል በቢሮዉ ስም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

 የኢትዮጽያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ በበኩላቸዉ ከተማችን አዲስ አበባ የኢትዮጽያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በምታደርገዉ ጉዞ  የአዲስ አበብ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ  ከኢቢሲ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት በተግባር ትብብሩን ማሳየቱ እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዉ ይህን ስኬታማ ጉዞ ዳር ለማድረስ  የነበረዉን ግንኙነታችንን በማጠናከር ባሉት በሚዲያ አማራጮቻችን ለመስራት  ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል ።

ሃላፊው አክለውም ይህ የስምምነት ፊርማ ዘላቂ ትስስርን የሚፈጥር እና  የከተማዋ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ጥራት ባለዉ መልኩ ለመስራት የሚያስችለን የጋራ አጀንዳችን ነዉም  ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.