“የመረጃ ምንጭ በመሆን የሃሳብ የበላይነትን ልን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“የመረጃ ምንጭ በመሆን የሃሳብ የበላይነትን ልንይዝ ይገባል”! ፡- አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ጋር በመሆን የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር፤ ስለ ከተማዋ የልማት ስራዎች በተደጋጋሚ መረጃ በመስጠትና ህብረተሰቡ በሚፈልገው ልክ የኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ሃፍታይ አክለውም ተቋማዊ አቅማችንን በማሳደግ እና የአርት ቡድኖችን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመጠቀም ከዚህ የተሻለ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መስራት ይጠበቅብናል" ብለዋል። 

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ከተማ እና ሃገር አቀፍ በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም በመሆን በዉጤት የታጀቡ በርካታ ስራዎችን ብንሰራም የዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታን በመረዳት በቅንጅት ፈጣንና ጥራት ያለዉ መረጃ መስጠት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ተናግረዋል፡፡ 

የቢሮዉ ምክትል ኃላፊ አቶ በትግሉ ኪታባ በበኩላቸዉ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ለህዝብ ፈጣን የመረጃ ምንጭ በመሆን እየሰራ ያለና ምንግዜም ኃላፊነቱ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዉ በቀጣይ ዉጤታማ ስራ ለመስራት ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም  እንደ አንድ የኮሙኒኬሽን ሰራዊት ተቀናጅተን በመስራታችን  ውጤታማ ተግባራት መከናዎናቸውን አቶ በትግሉ ኪታባ ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.