ዛሬ ማለዳ የከተማችንን የ6 ወራት የሥራ ጉዞ የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ የከተማችንን የ6 ወራት የሥራ ጉዞ የምንመዝንበትን የግምገማ መድረክ በይፋ ጀምረናል።

በዚህ የሦስት ቀን መርሃ ግብር፣ በ2018 በጀት ዓመት አጋማሽ በመንግሥትና በፓርቲ ሥራዎች የተከናወኑ አበይት ተግባራትን፣ ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደር ካለው አመራራችን ጋር በዝርዝር እንገመግማለን።

ባለፉት 6 ወራት፣ በ24/7 (ሃያ አራት ሰባት) የተለወጠ የሥራ ባህል፣ ነዋሪዎችንና የልማት አጋሮችን አስተባብረን በሁሉም ዘርፎች ያቀድናቸውን ሥራዎች በአማካይ 95.3% ማሳካት ችለናል።

ምንም እንኳን የላቀ ውጤት ብናስመዘግብም፣ የታዩ ጉድለቶችንና የተቋማትን ወጥ ያልሆነ የእቅድ አፈጻጸም፣ በተለይም ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ፣ አገልግሎት ለመስጠት ጉቦ መጠየቅ ፣ የቅንነት መጓደልን በግልጽ በመለየት  ለማረም የቀጣይ የትኩረት የምናደርግበት ይሆናል፣ እንዲሁም ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ተጨማሪ አቅምና ተሞክሮ የምንሰንቅበት እንዲሁም  የከተማችንን ነዋሪዎች በተሻለ ትጋትና ታማኝነት ለማገልገል  የምንዘጋጅበት መድረክ ነዉ።

ይህ ዉጤት እንዲመዘገብ የተጋችሁ ፣የደከማችሁ መላዉ አመራራችንና ሰራተኞችን እንዲሁም ያገዛችሁን የልማት አጋሮችን ከልብ አናመሰግናለን ።

በኅብር ሠርተን፣ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕያችንን ዳር እናደርሳለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.