“በትጋት አዲስ አበባን ወደ ላቀ ስኬት!” በሚል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“በትጋት አዲስ አበባን ወደ ላቀ ስኬት!” በሚል መሪ ሃሳብ ባለፉት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማችንን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ በስኬት አጠናቀናል።

በግምገማችንም አዲስ አበባን ፅዱ፣ አረንጓዴ እና ውብ፤ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ የተከናወኑ አበረታች ውጤቶችን አይተናል። ለአብነትም 134 ኪ.ሜ አዳዲስ መንገዶች የተገነቡ ሲሆን፣ ከ573 ኪ.ሜ በላይ መንገዶችም ጥገና ተደርጎላቸዋል።

በውሃና ፍሳሽ፦ የውሃ አቅርቦትን በ60 ሺህ ሜትር ኩብ ለማሳደግ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል። የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቱን በማዘመን ከተማችንን ከብክለት ለመከላከል የ8 ማጣሪያዎች ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።

ለህዝባችን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠትም በትምህርት፣ በጤና እና በተለያዩ ማህበራዊ ዘርፎች የህዝቡን አዳጊ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ 274 ፕሮጀክቶች ግንባታን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ስራዎችም ከተማችንን መልሰን እየገነባን፣ ከከተማችን አልፈን የሀገራችንን ገጽታ ቀይረናል። ለነዋሪዎቻችን 12 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችንም ገንብተን ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል።

የከተማችን የኮንፍረስ ቱሪዝም መዳረሻነት በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን ባለፉት 6 ወራት ከ150 በላይ ኮንፍረንሶች ተካሂደዋል። በስራ ዕድል ፈጠራ ከ195 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ለበርካቶች በጊዜያዊነት የስራ ዕድል የመፍጠር ስራ ተከናውኗል።

ከህዝቡ ቅሬታ ከሚቀርብበት የአገልግሎት አሰጣጥ አንፃርም በ’መሶብ’ የአገልግሎት አሰጣጥ የ94 % የህዝብ እርካታ ማግኘት መጀመራችን ለቀጣይ ስራችን ትልቅ ስንቅ ነው።

የበጎ ፈቃድ ተሳትፎም በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ከባለድርሻ የልማት አጋሮቻችን እና ከሕዝባችን 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማበርከት ከፍተኛ የሕዝብ አጋርነት የታየበትም ነበር።

በቀጣዮቹ 6 ወራትም ትኩረት የሚሹ የአመራር አፈፃፀም ልዩነቶችን ለማጥበብ፣ ተቋማዊ ግንባታን ለማጠናከር፣ ለቤት ግንባታ፣ ከተማችንን ለአለም አቀፍ ኩነቶች ይበልጥ ለማዘጋጀት ፣ ጉበኝነትና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊ አሰራር እና በህዝባችን ተሳትፎ ለማምከን፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመን እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ጫና ለመቀነስ የተጀመሩ ስራዎችን ለመቀጠል፣ የገቢ አሰባሰብን አጠናክረን ለመስራት የተግባባንበት ውጤታማ መድረክ ነበር ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.