ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የከተማዋን የልማት ኮሪደር ስራን አስመልክቶ ከተናገሩት:-
- የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን መነሻ በማድረግ በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ተሞክሮዎችን በመቀመር ከራሳችን ከተማ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የኮሪደር ልማት ተጠንቶ እንዲዘጋጅ በማድረግ ጥናቱ በየደረጃዉ ላሉ ባለድርሻ አካላት ቀርቦ በዉይይት የተገኙ ግብዓቶች ተካተው እንዲዳብር በማድረግ ለከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ቀርቦ እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡
- የጥናቱ ውጤት ያሳየን ጥናቱ በተደረገባቸው ኮሪደሮች ትላልቅ የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ያልተገናኙ መሆኑን ፣ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ መፈጠሩን፣ የከተማ ኘላን አተገባበርና የከተማ ስርአት መጓደልን በተለይም የፍሳሽና የጐርፍ ማስወገጃ ያለመኖር ፣ እንደ ሸረሪት ድር የተጠላለፈ የመብራትና የቴሌ መስመሮች ፣ የመፀዳጃና የማብሰያ ስፍራ እጥረት ወይም ያለመኖር ፣ ሰዎች በቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቆጥ ላይም ለመኖር የተገደዱበት፣ ለሰው ሰራሽና ለተፈጥሮ አደጋዎችም በተደጋጋሚ ተጋላጭ የሆኑበትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች መኖራቸውን
- በዚሁ መሰረት 48.7 ኪ.ሜ የሚሸፍን እና በተመረጡ የከተማችን አምስት ኮሪደሮች ማለትም ከ4 ኪሎ ፒያሳና የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ መልሶ ማልማት፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣ ከአራት ኪሎ መስቀል አደባባይ እና ቦሌ ድልድይ፣ በመገናኛ አስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን/ ኤግዚቢሽን ማእከል ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑ የመንገድ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናቀዉ አገልግሎቶቹን ለሕዝብ ክፍት ማድረግ እንዲቻል 24/7 እየተሰራ ይገኛል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.