"በበጀት ዓመቱ በ6 ወር ውስጥ የህዝባችን ጥያቄ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"በበጀት ዓመቱ በ6 ወር ውስጥ የህዝባችን ጥያቄ ምላሽ በመስጠት በትምህርት፣ በጤና እና በተለያዩ ማህበራዊ ዘርፎች የህዝቡን አዳጊ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ 274 ፕሮጀክቶች ግንባታን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል"። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👉 በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ስራዎችም ከተማችንን መልሰን እየገነባን፣ ከከተማችን አልፈን የሀገራችንን ገጽታ ቀይረናል። ለነዋሪዎቻችን 12 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችንም ገንብተን ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል።

👉 በውሃና ፍሳሽ፦ የውሃ አቅርቦትን በ60 ሺህ ሜትር ኩብ ለማሳደግ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል። የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቱን በማዘመን ከተማችንን ከብክለት ለመከላከል የ8 ማጣሪያዎች ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።

👉 አዲስ አበባን ፅዱ፣ አረንጓዴ እና ውብ፤ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ የተከናወኑ አበረታች ውጤቶችን አይተናል። ለአብነትም በበጀት አመቱ በ6 ወራት 134 ኪ.ሜ አዳዲስ መንገዶች የተገነቡ ሲሆን፣ ከ573 ኪ.ሜ በላይ መንገዶችም ጥገና ተደርጎላቸዋል።

👉 የከተማችን የኮንፍረስ ቱሪዝም መዳረሻነት በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን ባለፉት 6 ወራት ከ150 በላይ ኮንፍረንሶች ተካሂደዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.