ስሟን መኖር የጀመረችው አዲስ አበባ - አዲስ ም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ስሟን መኖር የጀመረችው አዲስ አበባ - አዲስ ምዕራፍ

አዲስ አበባ እንደ ከተማ ከተመሰረተች ከ135 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረች ሲሆን፤ ዛሬ ላይ ስሟን በሚመጥን የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች። 

የፌዴራል መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ በወሰዱት ቁርጠኛ አቋም፣ በኮሪደር ልማት የመዲናዋን ገጽታ ከመሰረቱ እየቀየሩት ይገኛሉ።

የኮሪደር ልማቱ ቀደም ሲል ተሽከርካሪዎች ብቻ ይሳለጡባቸው የነበሩ መንገዶችን ወደ ሰው ተኮር መሰረተ ልማት ቀይሯቸዋል። አሁን ላይ፦

• ሰፋፊና ምቹ የእግረኛ መንገዶች
• የሳይክል መንገዶች
• ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራቶችና የሕዝብ መናፈሻ ፓርኮች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

በመዲናዋ የሚኖሩት አና ዋልድማን የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጋ ለሲጂቲኤን (CGTN) በሰጡት ቃል፥ ልማቱ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ እንዴት እንደቀየረ አስተውያለሁ ብለዋል። "መሰረተ ልማቱ በመሟላቱ በየቀኑ በሳይክል ወደ ሥራዬ እጓዛለሁ" የሚሉት አና፣ ከልጆቻቸው ጋር በምሽት በነጻነት በእግር መንቀሳቀስና በመዝናኛ ስፍራዎች ጊዜ ማሳለፍ መቻላቸው ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገራሉ።

ሌላኛው በመዲናዋ የተከናወነው አስደናቂ ሥራ  የወንዝ ዳርቻ ልማት ነው። የተበከሉ ወንዞች ተጸድተው፣ ዛሬ ለዓይን የሚማርኩና ንጹህ አየር የሚገኝባቸው የቱሪስት መዳረሻዎች ሆነዋል። 

የቱሪስት አስጎብኚ ድርጅት ባለቤቱ አቶ ተስፋየሱስ ያቆብ እንደሚሉት፤ ይህ ልማት "የት እንደነበሩ የማይታወቁና የተደበቁ" የከተማዋን ውበቶች ገልጦ አውጥቷል። የወንዝ ዳርቻ ልማቱ አዲስ አበባን በከተማ ቱሪዝም መዳረሻነት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትታወቅ እያደረጋትም ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት አሥተዳደር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር  ከድር አደም እንደሚሉት፣ ይህ ሥራ የከተማዋን መጨናነቅ ከመቀነስ ባለፈ ጤናማ አኗኗርን የሚያበረታታና ለቀጣዩ ትውልድ የሚሸጋገር ታላቅ አሻራ ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.