"የህዝብን አደራ ተቀብለን፤አቅደን እና ትኩረት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የህዝብን አደራ ተቀብለን፤አቅደን እና ትኩረት ሰጥተን፤ተቀናጅተንና ተናበን በሰራናቸዉ ስራዎች በአማካይ በሁሉም ዘርፎች 95.3 በመቶ መፈፀም ችለናል፡፡"ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ይህ የተባለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት ነዉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳናች አቤቤ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ከተማ አስተዳደሩ እና የከተማዉ ምክር ቤት በአደረጉት ጠንካራ እና ወጥነት ያለዉ የክትትል እና ድጋፍ ስርዓት ግምገማ የተረጋገጡ እዉነታዎች ናቸዉ ብለዋል፡፡

በተለይም ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ ያለዉ የአመራር መዋቅራችን ጠንካራ ዉህደት በመፍጠር እና የዉሳኔ ሰጭነትን በማሳደግ በመልካም አስተዳደር የታቀዱና ህዝቡ ሲያነሳቸዉ ለነበሩ ጥያቄዎች ተጠያቂነትን በማስፈን ምላሽ እየሰጠ የመጣበት ባህል እያደገ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ከሁሉ በላይም አመራሩ የስራ ስምሪት በመስጠት በሚጨበጥ የስራ አፈፃፀም ሰዉን በስራ ብቻ መመዘን እና እዉቅና መስጠት ሌለኛዉ ለዉጤት መምጣት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት በየደረጃዉ የምንገኝ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች የህዝብን አደራ በመቀበል ፤አቅደን እና ትኩረት፤ሰጥተን ተቀናጅተንና ተናበን በሰራናቸዉ ስራዎች በአማካይ በሁሉም ዘርፎች 95.3 በመቶ መፈፀም ችለናልም ብለዋል፡፡

እነዚህ ስኬቶቻችን ከከተማችን ፈጣን እድገት እና ከህዝባችን የመልማት ጥያቄ ለቀጣይ 6 ወራት የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ አቅም የፈጠርንበት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ታላላቅ ድሎች ዝግጁነታችንን ያረጋገጥንበት ነዉ ሲሉም ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.