ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በብስክሌት መንገድና በመሮጫ ትራክ በተሽከርካሪ በመሄድ ልማቱን ያበላሸው አሽከርካሪ 100 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ራስመኮንን አካባቢ በቀን 17/05/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት አካባቢ አራዳ ፓርክ ውስጥ በብስክሌት መንገድና በመሮጫ ትራክ ላይ መኪና በማሽከርከር መሰረተ-ልማቱን ያበላሸው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር በማዋል 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት አሽከርካሪው ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን ተገልጿል ።
ባለስልጣኑ ጥቆማ ለሚሰጠው ህብረተሰቡ ታላቅ አክብሮት እንዳለው በመግለፅ ጥቆማ ለሰጠው እያመሰገነ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማት፣ በወንዞች ዳርቻና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን ጉዳት በሚያደርሱት እና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ በመቀጠል ሀላፊነቱ እንዲወጣ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.