ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የመንግስት ሀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የመንግስት ሀብትና ንብረትን ከብክነት መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የኦዲት ፎረም ጉባዔውን አካሄደ።

በከተማችን ውስጥ ያሉ የመንግስት ተቋማት ህግና ስርዓት ተከትለው እንዲተዳደሩና ሀብትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲያውሉ ትልቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው እንደመሆኑ መጠን የተሰጣቸውን ኃላፊት እና ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በመክፈቻ ንግግራቸው ጠቁመዋል ። 

አክለውም  ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የመንግስት ሀብትና ንብረትን ከብክነት መከላከል እንደሚገባ በመጠቆም የምክር ቤቱ ኦዲት ፎርም የተቋማት የኦዲት ግኝት አጣሪ ኮሚቴ በማቋቋም በሁለት ዙር ባካሄደው የማጣራት ስራ የኦዲት ግኝት መገኘቱንም ገልፀዋል፡፡
 
አፈ ጉባኤና የኦዲት ፎረም ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ለዓመታት ሲንከባለል የቆዩት ችግሮች ለማስተካከል የተደረገው ጥረት የአመራር ቁርጠኝነት ታክሎበት ውጤት ሊመጣ እንደቻለ በመግለፅ በቀጣይ  ህጉንና ስርዓቱን  ያማከለ ስራ በመስራት የጋራ መግባባት በመፍጠር  የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ከግብ ማድረስ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻ በኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ ለወሰዱ ተቋማት የምስጋናና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላችዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.