ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የከተማዋን የልማት ኮሪደርን አስመልክቶ ከተናገሩት:-

👉ለንግድ ቤቶች እና ለግል ባለይዞታዎች ምትክ መሬትና የካሣ ክፍያዎችን መፈጸም፣ የልማት ተነሺዎች ወደ ተዘጋጀላቸው የመኖሪያና የመስሪያ ቦታ የሚያጓጉዝ ትራንስፖርት ማዘጋጀት ፣ በገቡበት አካባቢ ልዩ አቀባበል እየተደረገላቸው ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ትስስራቸው ተጠብቆ የማዘዋወር ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና የኃላፊነት ስሜት ተከናውኗል

👉ግልፅና ዝርዝር የማስፈጸሚያ እቅድ በማዘጋጀት የዲዛይን ዝግጅት፣ በጀትና ለልማት ተነሺዎች መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ መስሪያ ቦታና ምትክ መሬት የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል፡፡

👉ከመኖሪያ እና መስሪያ ቦታቸዉ የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን መረጃ ማደራጀት፣ ተነሺዎችን ማወያየት፣ በምርጫቸዉ መሰረት በተቀላጠፈ አግባብ የሚስተናገዱበት ስርዓትና የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተዘርግቶ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

👉የልማት ተነሺዎች የገቡባቸዉ የመኖሪያ ቤቶች የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው ስለመሆኑና የቅርብ ክትትል በማድረግ ተነሺዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡

👉የከተማው ከፍተኛ አመራር የመኖሪያ ቦታዎችን ሁኔታ እና የልማት ተነሺዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመጎብኘትና አገልግሎት ስለመሟላቱና ጉድለቶችም ካሉ ለማረም የሚያስችል ጉብኝት በሁሉም ሳይቶች ላይ በተደጋጋሚ አድርጏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.