በሁሉም ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ከተማ፥ ውብ አዲስ አበባ!
ከተማችን አዲሰ አበባ፣ እያሰመዘገበች ያለውን ከፍተኛ ዕድገት ተመራጭ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ በተለይም የቱሪዝም መስህብነት የሚያሳድጉ የሚያልቁ፥ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች፣ ዘመናዊ ማዕከላት፣ ፓርኮች ፣ ቅርሶች እና ሙዚየሞች ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የሞተር እና ሞተር አልባ ተሽከርካሪ መንገዶች ፣ የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች እና የትራንስፖርት አማራጭን ጨምሮ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ እና ደረጃቸውን የጠበቁ ፕላዛዎች ለጉብኝት እና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተማራጭ ከተማ እንድትሆን አስችሏታል።
በተጨማሪም፣ ሀገር በቀል እጽዋት መገኛ የሆነው ጉለሌ እጽዋት ማዕከል ጨምሮ የከተማዋን ዙሪያ የከበቡ ታሪካዊ ዋሻዎችና ቅርሶች የጎብኚዎች ቀልብ እንዲያርፍባት አድርጓል፡፡
በሌላ በኩል በመዲናዋ የተሰሩ ዘርፍ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው የጎላ ሰው ተኮር ልማቶች፣ በአለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ በቀዳሚነት ስሟ እንዲጠቀስ አድርጓል፡፡
አዲስ አበባ በፍጥነት እያስመዘገበች በምተገኘው አስደማሚ ለውጦች በርካታ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ኩነቶችን እና ኮንፍረንሶችን በማዘጋጀት ተወዳዳሪ ከተማ ሆናለች፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.