የጥንቃቄ መልእክት ከአዲስ አበባ ፓሊስ!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጥንቃቄ መልእክት ከአዲስ አበባ ፓሊስ!

በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ እና የመንግስት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው  ፓርኮች መካከል እንጦጦ ፓርክ ይጠቀሳል። ፓርኩ  የቱሪስት መዳረሻ፣ የከተማችን ነዋሪ መዝናኛ እና ጤናውን ለመጠበቅ ስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያደርግበታል። 

ሆኖም ይህን የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ተከትለውና ጎብኚ ስፓርተኛ በመምሰል ወይም ደግሞ በአሳቻ ስፍራ በመደበቅ ወንጀል እየፈፀሙ እንዳሉ ህብረተሰቡ ሲያነሳ ይስተዋላል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ፓሊስ ባደረገው ክትትል በዛሬው ዕለት ከታች በምስሉ የሚታዩት ሶስት  ግለሰቦች ሽሮ ሜዳ ቁስቋም አካባቢ ወደ እንጦጦ የሚገቡ የፓላንድ ዜጎች ሊዘርፉ ሲሉ ደርሶ አሳዶ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።  በምርመራውም አንዱ ፎርጅድ የመከላከያ መታወቅያ ይዞ የተገኘ ሲሆን የሁለቱን እያጣራ ይገኛል። ተጠርጣሪዎቹ ከፓሊስ ለማምለጥ ሲሮጡ እና ሲዘሉ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ለማወቅ ተችሏል። 

ህብረተሰቡ መሰል ጥርጣሬዎችን በመከታተል ትብብር እንዲያደርግ  አከባቢውን እንዲጠብቅ እና ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል አሳስቧል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.