#የጠሚሩምላሾች

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

#የጠሚሩምላሾች

ኢኮኖሚ ጉዳዮችን በሚመለከት

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ከያዛቸው ዋነኛ ዓላማዎች መካከል አንደኛው የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን ማረጋጋት ነው። ሁለተኛው የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍና ብዝሃ ተዋናይ በማሸጋገር ጥራት ያላው እድገት ማስመዝገብ ሲሆን ሌላኛው የኢትዮጵያን የእዳ ጫና ማቃለል ነው። በዚህ ረገድ በሁሉም መመዘኛ በኢትዮጵያ አመርቂ የኢኮኖሚ ስኬት ተመዝግቧል።

ነገን መገንባት 

በቴክኖሎጂ ፣ በህጻናት ትምህርት፣ ከተማ ልማት እና አረንጓዴ ዐሻራ የሰራናቸው ስራዎች የእኛ መንግስት የትናንትና እዳ ለመቀነስ እና ዛሬን እድገት ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ልጆቻችን ነገ ቀና ብለው ከስደት ተቆጥበው በሀገራችን ሀብት ማፍራት እንዲችሉ በእውቅት እየተመራ መሆኑን ያሳያል።

“ኢትዮጵያ ያሳየቸው የኢኮኖሚ እድገት በማንም መመዘኛ ፊት አከራካሪ አይደለም፡፡” 

የእድገት ትንበያ

ኢትዮጵያ ነዳጅ ሳይኖራቸው ቀዳሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በዘንድሮው በጀት ዓመት ያለፉት ስድስት ወራት የእድገት አፈጻጸም በመገምገም ኢትዮጵያ በዓመቱ መጨረሻ የ10 ነጥብ 2 በመቶ እድገት እንድምታስመዘግብ የእቅድ ማሻሻያ ተደርጓል። ይህ ትንበያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ ጋር የተቀራረበ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት 999 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት መሰብሰብ ተችሏል። ይህም ከዓመቱ እቅዳችን 78 በመቶ የሚሸፍን ነው። በተለይ በሰብል በሆረቲ ካልቸርና በጥጥ ከእቅድ አንጻር 79 በመቶ ማሳካት ተችሏል። በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ይህን አጠናክሮ መቀጠል ከተቻለ ከእቅድ በላይ ማሳካት ይቻላል።

የገቢ እድገት

የበጀት ዓመቱ ሲጀመር መንግስት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ ባለፉስ ስድስት ወራት ብቻ 709 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል። ይህም ትልቅ አፈጻጸም ቢሆንም ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ግን አሁንም ብዙ መስራት እንዳለብን ያሳያል። ከወጪ አንጻርም መንግስት በስድስት ወራቱ ለማውጣት ካቀደው ገንዘብ 48 ነጥብ 5 በመቶ ብቻ ወጪ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ሲጀመር የኢትዮጵያ ኢንዱስትርዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ አይበልጥም ነበር ይህን አሁን በሶስት ዓመት ብቻ 66 ነጥብ 3 በመቶ ማሳደግ ተችሏል። ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የኢንዱስትሪዎች የኢነርጂ አጠቃቀም 16 በመቶ አድጓል። በንቅናቄው አማካኝነትም 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶለር ያወጡ የነበሩ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ተችሏል። ከኢንዱስትሪ የሚገኘው የወጪ ንግድም የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ በእጥፍ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያዊያን ሃብት ብቻ የተገነባ ታላቅ ፕሮጀክት
የህዳሴ ግድብን  ያለ አንድ ብር እርዳታና ብድር ያሳካ መንግስት ፕሮጀክት አይሰራም ሊባል አይችልም። በህዳሴ ላይ አንድ ብር እርዳታ ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም፤ በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ቁርጠኛ አቋም ጨክነው በጋራ ቁመው ስለሰሩ የተከወነ የጋራ ፕሮጀክት ነው።

#የጠሚሩምላሾች 
#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.