ህዳሴ ግድብ

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ህዳሴ ግድብ

የማዕድን ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ያለፉት ስድስት ወራት የ30 በመቶ የገቢ ጭማሪ አሳይቷል። የብረት ምርት 36 በመቶ እንዲሁም ሲምንቶ ምርት 28 በመቶ ጨምሯል። ይህም በተለይ የቤት ልማት እየተስፋፋ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው።

“በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ:አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም::በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨክነው በጋራ ቁመው ስለ ሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት ነው"::

ከውጭ የሚመጡ ዜጎች  ከሰላምታ በመቀጠል በአዲስ አበባ  ውበት በመደነቅ ይጠይቁናል 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች ከሰላምታ በመቀጠል ቀጣይ ንግግራቸው  በአዲስ አበባ  የተሰራውን በማድነቅ እንደዚህ ያለች ወብ ከተማ መሆኗን  አልገመትንም የሚሉ ዜጎች ገጥመውናል"፡፡

የወጪ ንግድ አፈጻጸም

ባለፉት ስድስት ወራት ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 5 ነጥብ 1  ቢሊዮን ዶላር  ገቢ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከእቅዱ አንጻር የ120 በመቶ አፈጻጸም ያሳያል። ከአገልግሎት ወጪ ንግድም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር እንዲሆም ከሃዋላ 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በስድስት ወራት ውስጥ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር  የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት  በመሳብም የተሳካ የማክሮ ኢኮኖሚ ስራ ተከናውኗል።


እዳ ቅነሳ 

ይህ መንግስት አንዱ ክብር የሚያሰጠው ስራ እዳ ላይ የሰራው ስራ ነው። በለውጡ ጅማሪ ኢትዮጵያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ የነበረች ሀገር ናት። ከለውጡ በኋላ ይህ መንግስት አንድ ዶላር የንግድ ብድር ስምምነት አላደርገም። ይህ ከፍተኛ ምስጋና የሚገባው ጠንካራ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው። የንግድ ብድር ያበደሩን ወዳጆቻችን “ብድሩ ተገቢ አይደለምና ወደ ትክክለኛው የብድር ስርዓት መመለስ አለበት” በሚል ባለፉት ሁለት ሶስት ዓመታት ከፍትኛ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል።  ከሞላ ጎደል ይህ ጥረት ተሳክቶልናል።

የሰላም ጉዳይ 

ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም እጦት እንድንኖር ካደረጉን እና ካልተላቀቅንባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው ከጥንት የተጠባነው ልዩነቶችን በሃይል ብቻ  የመፍታት ልምምድ ነው። ሁለተኛው  ደግሞ አሁንም ከጥንት የመጣ የባንዳነት ልምምድ ሲሆን ሶስተኛው የጠላቶቻችን ኢትዮጵያ ካደገች የሚል ያልተቋረጠ ስጋት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.