በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ / ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት አባላት በምክር ቤቱ ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤ ላነሷቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ :-
አዲስ አበባ አገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃዋን ከሚመጥናት ደረጃ ላይ እንድትደርስ ፣ ስሟንና ግብሯን የማገናኘት ተግባር ነው እየተከናወነ ያለው
ከለወጡ ጊዜ ጀምሮ የከተማችንን ገፅታ ለማሻሻል በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።
የኮሪደር ልማቱም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን እና ምሁራንን ባሳተፈ አግባብ በቂ ጥናት ተደርጎበት ተግባራዊ መደረግ የጀመረ እና 7 / 24 እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት ነው።
ተቋማት እና ግለሰቦች ለከተማችን ልማት ተባባሪ ናቸው ፤ ከኤንባሲዎች ጋር ተያይዞ ያለውን ጉዳይም በመወያየት እንዲሁም በሂደት የከተማዋን ገፅታ ለመቀየር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን እንዲገነዘቡ በማድረግ እየተፈታ ስራዎቻችን ለአፍታም ሳይቋረጡ ይቀጥላሉ።
ፕሮጀክቱ የከተማችንን ገፅታ በእጅጉ ይቀይራል።
ትራንስፖርትን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን ያሳልጣል።
አዲስ የስራ ባህል እየገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው::
የልማት ኮሪደሩ ሲጠናቀቅ የከተማችን ኢኮኖሚም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።
በልማት ኮሪደሩ ያለው ተሞክሮ ከሰፋ ከተማችን ወደ ተሻለ ደረጃ ትደርሳለች ።
የተከበሩ የምክር ቤት አባላት የሰጡንን ገንቢ ሀሳቦች በሌሎች ስራዎቻችንም ተግባራዊ እናደርጋለን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.