#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

የወልቃይት አካባቢ የተፈናቃዮች ጉዳይ

የወልቃይት አከባቢ ነዋሪዎች በሰላማዊ መንገድ የመኖር መብት አላቸው። ይህን የፌደራል መንግስት በጽኑ የሚያምነው ጉዳይ ነው። ነገር ግን የአማራና የትግራይ ክልሎች በወልቃይት ጉዳይ ለረዥም ጊዜ የይገባኛል ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተዋል። ሆኖም  የፌደራል መንግስት እያለ ያለው ሰው አይፈናቀል ባለበት ይመለስ፤ ራሱን ያስተዳደር፤ ራሱ ጥያቄውን ይመልስ ነው። ማንም ከውጭ ሆኖ ሊወስንለት አይገባም።
የዘንድሮውን ምርጫ በሚመለከት

የዘንድሮው ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሃዊና አካታች እንዲሁም ካለፈው ምርጫ የተሻለ እንዲሆን መንግስት አበክሮ እየሰራ ነው።

 ምርጫውን በሚመለከት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለኝ መልስ በውጤት እንየው ነው። በእርግጠኝነት መናገር የምፈልገው ጉዳይ ይህ ፓርላማ በብዙ መልኩ በርካታ ድምጾች የሚሰሙበት ይሆናል። ምርጫው በሰላም ይከናወናል፤ በምርጫ የሚሳተፉ ሃይሎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ።

አካታች ሀገራዊ ምክክርን በሚመለከት

ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ጦርነትን ሰርተዋል፤ የአሁኑ ትውልድ ደግሞ በውይይት ሀገርን መስራት፣ መገንባት አለበት። ከዚህ አኳያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳዎችን ለይቷል። የተሻለ ስራም ሲያከናውን ቆይቷል። በቀጣይም በርካቶችን ባካተተ መልኩ አጀንዳዎቹ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ሃሳቦችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። እስካሁን ባለው ሂደትም ኢትዮጵያዊያን የተቀራረበ ፍላጎት እንዳላቸው ትምህርት የሰጠ ነው።

#የጠሚሩምላሾች 
#PMOEthiopia

#የጠሚሩምላሾች 
#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.