በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት አባላት በከተማው በተሰሩ በርካታ ስራዎች ፤ እየተሰሩ ባሉ እና ቀጣይ የሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ የሰጣቸው ማብራሪያዎች፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር በተመለከተ
ለ 325 ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት 5.287 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል።
ከ 110 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመጠባበቂያ ምግብና ቁሳቁስ ክምችት ተዘጋጅቷል።
የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት በተመለከተ
የቆየውን የሲስተም መቆራረጥ ችግር የሚፈታ አዲስ ቴክኖሎጂ ወደ ሥራ ገብቷል።
በዚህም ለ 805,432 ነዋሪዎች ቀልጣፋ የነዋሪነት አገልግሎት ተሰጥቷል።
ትራንስፖርት ዘርፍ በተመለከተ፤-
ባለፉት 6ወራት 14,133 ተሸከርካሪዎችን በማሰማራት በቀን በአማካይ 3.98 ሚሊየን ህዝብ በማጓጓዝ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ማሳለጥ ተችሏል፡፡
የብዙኃን ትራንስፖርት ድርሻ ከነበረበት 36 በመቶ ወደ 42 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፤
የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ከማስፋፋት አኳያ የከተማውን የትራንስፖርት ችግር በወሳኝነት ሊቀርፍ የሚችል የፈጣን አውቶብስ ትራንዚት የBRT B2 ፕሮጀክት የ15.6 ኪ.ሜ የመንገድና የዴፖ ግንባታ ስራም ተጀምሯል፡፡
የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ከማስፋፋት አኳያ በኮሪደር ልማት የተገነቡትን 241 ኪ/ሜትር የብስክሌት ኦፕሬሽን ስራ ለማስጀመር 10 ኦፕሬተሮች የምዝገባ ፍቃድ ወስደው ሶስቱ ብስክሌቶችን ከውጪ የማስገባት ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡
ባልተገባ የመንገድ አጠቃቀም የሚከተሉ አሽከርካሪዎችና እግረኛ የመንገድ ተጠቃሚዎችን የመቆጣጠርና አስተማሪ እርምጃዎችን የመዉሰድ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
የትራፊክ ቁጥጥር እና የፓርኪንግ አስተዳደር ክፍያ ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ አገልግሎቱን ማዘመንና ማሻሻል ተችሏል፡፡
የኪነ-ጥበብ ዘርፍን በተመለከተ
በኪነ-ጥበብ የዘርፉን አቅምና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያሳድጉ የሚችሉ 380 የሥነ ጽሁፍ ሥራዎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ መፈፀም ተችሏል፡፡በዚህም እጅግ ዘመናዊ የትያትርና ፊልም ማእከላትን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡
25 የሚሆኑ የዕይታዊ ጥበባትና ክውን መልቲ-ሚዲያ ሥራዎች የስዕል ኤግዚቢሽኖች፣ ቶክ-ሾውና ስልጠናዎችን ተካሄደዋል፡፡
እንዲሁም በከተማዋ መንግስታዊ ኩነቶችን ተከትሎ 245 የሚሆኑ የኪነ-ጥበብ መድረኮችና ኩነቶችን ማዘጋጀትና ማስተባበር ታቅዶ 100% መፈፀም ተችሏል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.