"የልማት ተነሺዎች የገቡባቸዉ የመኖሪያ ቤቶች መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የልማት ተነሺዎች የገቡባቸዉ የመኖሪያ ቤቶች መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው ስለመሆኑና የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡!" ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከተናገሩት የተወሰደ

የልማት ተነሺዎች የገቡባቸዉ የመኖሪያ ቤቶች የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው ስለመሆኑና የቅርብ ክትትል በማድረግ ተነሺዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም የከተማው ከፍተኛ አመራር የመኖሪያ ቦታዎችን ሁኔታ የልማት ተነሺዎች አገልግሎት ስለመሟላቱና ጉድለቶችም ካሉ ለማረም የሚችል ጉብኝት በሁሉም ሳይቶች ላይ አድርጓል፡፡ ከመሰረተ ልማትና ከስራ እድል የሚያያዙ ጉድለቶችንም እንዲታረሙ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

የኮሪደርና የመልሶ ማልማቱ ለከተማችን ነዋሪዎች ካስገኛቸዉ እና ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከሚኖረዉ ፋይዳዎች መካከል በልማቱ ምክንያት ተነሺ የሆኑ እጅግ በጎሰቆሉና ለመኖር በማይመቹ ቤቶች፣ ለተደጋጋሚ የእሳትና የጎርፍ አደጋ እንዲሁም ለብክለት ሲዳርጉ የነበሩ የመሰረተ ልማት ጉድለቶች ባሉበት ሁኔታ ሲኖሩ የነበሩ የበርካታ ከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ቤት አግኝተዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.