በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት አባላት ባለፉት 6 ወራት በከተማው በተሰሩ በርካታ ስራዎች ፤ እየተሰሩ ባሉ እና ቀጣይ የሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ የሰጣቸው ማብራሪያዎች፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት በተመለከተ

👉ቋሚ ሥራ፦ ለ 195,112 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ::

👉ጊዜያዊ ሥራ፦ በኮሪደር እና በቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች 250,000 በላይ ሰዎች ጊዜያዊ ሥራ አግኝተዋል።

👉የዘርፍ ድርሻ፦ የአገልግሎት ዘርፍ (71%) ትልቁን ድርሻ ሲይዝ፣ ኢንዱስትሪ (21%) እና ግብርና (8%) ይከተላሉ።

👉ስልጠና፦ 266,962 ሰልጣኞች በክህሎት መር አጫጭር ስልጠናዎች ሰልጥነዋል።

👉ተጠቃሚዎች፦ ሴቶች 53.7%፣ ወጣቶች 49.25%

አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ:-

የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በተሰራው ስራ 23 አዳዲስ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማስደገፍ 370 አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል።

በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲለሙ በማድረግ፤ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይን እርካታ 94.2% ማድረስ ተችሏል።

በአገልጋዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከተነሱ የተገልጋይ ጥያቄዎች መካከል 86% የሚሆኑት ችግሮች መፈታታቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል።

በተቋማት ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር 183 የህጻናት ማቆያ፣ 1ዐዐ የሰራተኞች ካፊቴሪያ እና 166 የሸማቾች ሱቆች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

ተጠያቂነት ከማስፈን አንፃር በ61 አመራሮች፤ በ126 ዳይሬክተር፤ ቡድን መሪዎችና ከ3ሺ በላይ ሰራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ በፈፀሙት ጥፋት ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡

የገቢ ግብር አሰባሰብን በተመለከተ

95% የግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ የተደረገ ሲሆን በ6 ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 176.03 ቢሊዮን ብር ውስጥ 162.72 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 92.4% መፈፀም ተችሏል፡፡ ይህም ከ2017 ጋር ሲነፃፀር 51.12 ቢሊዮን ብር ( 45.8%) የገቢ ጭማሪ አሳይቷል ::

የግማሽ ዓመት ወጪ አፈጻጸም በተመለከተ ከጠቅላላ ወጪ፡ 148.9 ቢሊዮን ብር የካፒታል ወጪ ድርሻ 70.14% ፤ በማህበራዊ ድጋፍ ቀጥታ ድጎማ 18.72 ቢሊዮን ብር ፤ እንዲሁም ለተማሪ ምገባ ፣ ለዩኒፎርም፣ ለጤና መድህንና ለትራንስፖርት 55.7 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ 59.7% የእድገት መጠን ማሳየት ተችሏል፡፡

የቅሬታ አያያዝና አገልግሎት ክትትል በተመለከተ ከከንቲባ ጽ/ቤት ጀምሮ ግልፅ የቅሬታ ስርዓት በመዘርጋት፤ በብልሹ አሰራርና ሌብነት የተሳተፉ 282 ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ተወሰዷል፡፡

በቴክኖሎጂ በተደገፈ የቁጥጥር ስራ በ7,678 ግብር የሚሰውሩ ነጋዴዎችና በ2,261 የጭነት መኪናዎች ያለ ደረሰኝ ምርት ሲያጓጉዙ በመገኘታቸው ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ከተማዋ በገቢ አሰባሰብና በጀትን በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር ከአፍሪካ ከተሞች ጋር በተካሄደ ጥናት ምዘና መሰረት ከተማችን ቀዳሚ በመሆን ልምዷን አካፍላለች፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.